120K+ Population
4 Tourism Sites
7 Cultural Values
3 Languages
Our Story

ስለ ጅሌ

በታሪክ፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በባህላዊ ቱፊቶች የበለጸገ ማህበረሰብ

ታሪካዊ ዳራ

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የስም ስያሜዋን ያገኘችው የወረዳው ነዋሪዎች ከሆኑ ከአምስቱ ጅሌ እና ሱባ ጥሙጋ ሲሆን ጅሌም ሆነ ጥሙጋ በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ አባቶች ስም እንደሆነ ከሽማግሌዎችና እድሜ ጠገብ አባቶች የተገኙ ታሪኮች ያወሳሉ፡፡

ይህ ወረዳ በዚህ ስያሜ መጠራት የጀመረው በደርግ ስርዓተ መንግስት የወረዳዎችና ዞኖች ምስረታ ወቅት እንደሆነና በሰሜን ሸዋ ክፍላ ሀገር ይፋትና ዱሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ጅሌ ወረዳ በመባል እንደምትታወቅ የተለያዩ በጽሁፍ የሚገኙ ድርሳኖችና መጻጽፎች እንዲሁም አፈታሪኮች ያሰረዳሉ፡፡

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ይህን አሁን የምትጠራበትን ስያሜ ራሷን ችላ ያገኘችው ከ1986 ዓ/ም መባቻ ላይ ከኤፍራታና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ከተለየችበት ጊዜ አንስቶ ሲሆን የወረዳዋ ዋና ከተማ ሰንበቴ በማድረግ ተመሰረተች፡፡ በ1987 ዓ/ም የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ራሱን ችሎ በተመሰረተበት ወቅት ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጋር በመቀላቀል አርጡማ ጅሌ የሚል ስያሜ ተስጥቷት እስከ 1993 ዓ/ም መቆየቷም ይነገራል፡፡ የስሟ ስያሜ እንደየወቅቱና ነባራዊ ሁኔታ ሲቀያየር መጥቶ ከ1993 ዓ/ም መባቻ ላይ ከአርጡማ ጅሌ ወረዳ በመለየት ራሷን ችላ ዛሬ ለምትጠራበት ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ስያሜ ላይ ደርሳለች፡፡

እምነትና ቋንቋ

በወረዳዋ ውስጥ ከሚኖረው ማህበረሰብ 99% የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን 1% የሚሆኑት የተለያየ እምነት ተከታይ እንደሆኑ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ከቋንቋ አንፃር 95% ኦሮሚኛ ተናጋሪ ሲሆኑ 5% አማርኛ ተናጋሪ ናቸው፡፡

አካባቢ እና ስነ-ህዝብ

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የምትገኘው በአብክመ በኦሮሞ አስተዳደር ዞን ውስጥ በሰሜን ከአርጡማ ፉርሲ፣ በደቡብ ቀወት ወረዳና ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር፣በምዕራብ ኤፍራታ ግድምና ቀወት ወረዳ እንዲሁም በምስራቅ የአፋር ክልል ወረዳዎች ሀደለኢላና ሰሙ ሮቢ የምትዋሰን ሲሆን ከሀገራችንና መዲናችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ በስተሰሜን 265 ኪ.ሜ እርቃ ወደ ደሴ በሚወስደው በትልቁ አውራ መንገድ ላይ የትገኛለች፡፡ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር በስተምስራቅ 765 ኪ.ሜ እርቃ የምትገኝ ሲሆን፣ ከዞኑ መቀመጫ ከተማ ከሆነችው ከሚሴ በስተደቡብ በዋናው የደሴ አድስ አበባ መንገድ ላይ 63 ኪ.ሜ ላይ ትገኛለች፡፡

የአየር ሁኔታና የመሬት አቀማመጥ

የወረዳዋ አየር ንብርት 97% የሚሆነው በቆላማነት የሚታወቅ ሲሆን 3% የሚሆነው ወይና ደጋ ነው፡፡ የአየር ሙቀቷም ዝቅተኛው 240c ሲሆን ከፍተኛው 330c ነው፡፡ የወረዳዋ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ2,000- 2,600 ሚ. ሊ. እንደሆነ የወረዳዋ የአየር ንብረት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የዝናብ ወቅቶችም ክረምትና በልግ ሲሆን የክረምቱ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም የሚቆይ ሲሆን የበልጉ ወቅት ከየካቲት እስከ ሚያዚያ የሚቆይ ይሆናል፡፡ የወረዳዋ የመሬት ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ከ500-700 ሜ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ የወረዳዋ የቆዳ ስፋት 88,256 ሄ/ር ሲሆን የመሬት አቀማመጧም 31,052 ሄ/ር የሚሆነው ተራራማና ዳገታማ ሲሆን 57,204 ሄ/ር የሚሆነው ሜዳማ ነው፡፡ ከዚህ የመሬት አቀማመጥ ውስጥ 12,000 ሄ/ር የሚሆነው ለእርሻ መሬት የሚያገለግል ሲሆን 25,280 ሄ/ር የሚሆነው በደን ተሸፍኖ ይገኛል፡፡

የህዝብ ብዛትና የአኗኗር ሁኔታ

የሀገሪቱ የ1997 ዓ/ም ስታስቲክሳዊ የህዝብ ቆጠራ ውጤት (Census) መሰረት በማድረግ አሁን ላይ የወረዳዋ ህዝብ ቁጥር 65,873 ወንድ 67,479 ሴት በድምሩ 133,352 እንደሚሆን የገመታል፡፡ ከዚህ የህዝብ ቁጥር ውስጥ 88% የሚሆነው ኑሮውን በግብርና የሚመራ ሲሆን 12% የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማራ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ትምህርት ያለበት ሁኔታ

በትምህርት መስክ ወረዳው ከዘውዳዊ አገዛዝ ጀምሮ ለዘመናት ወደ ኋላ ቀርቶ የነበረና በዚህም ምክንያት ማህበረሰቡ ልጆቹን በወቅቱ ማስተማር ባለመቻሉ እንደ ማህበረሰብ ንቃተ ህሊናው በትምህርት የዳበረ ትውልድ የመፍጠር ራዕይ ጊዜ ሊወስድ እንደቻለ ማየት ተችሏል፡:

በመሆኑም ይህንን ጉድለት ለመሙላት በተሄደው ርቀትና በተሰራው ስራ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 3 የ2ኛ ደረጃ ት/ት ተቋም፣ 46 ከ1-8ኛ ክፍል ማስተማር የሚችሉ ተቋማትና እንዲሁም የቅድመ መደበኛ ት/ትን ጨምሮ በጥቅሉ 50 የትምህርት ተቋማትን በመገንባት መማር ካለባቸው 26,364 ህጻናት ውስጥ 20,264 ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በማድረግ የወረዳው የትምህርት ሽፋን 77% ላይ እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል፡፡

የጤና ዘርፍ

ጤናማ ማህበረሰባ በመፍጠር አምራች ዜጋን እውን የማድረግ ራዕይን በተግባር ለማሳየት መተሄደው ርቀት የጤና ተቋማትን በስታናዳርዱ መሰረት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚሁ አግባብ 4 ጤና ጣቢያዎች ተገንበተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደወረዳ 20 የጤና ኬላዎች መኖር ሲገባ 19 እንዲኖር ማድረግ ተችሏል፡፡ በጥቅሉ የተቋማት ማስፋፋት፣የግብዓት አቅርቦት፣የአገልግሎት አሰጣጥና የሰው ሀይል ስምሪትን ጨምሮ የተሳለጠ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በተሰራው ስራ የወረዳውን የጤና ሽፋን 86% ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡

ንጹህ ውሃ አቅርቦት

ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በተሄደው ርቀት 218 የውሃ ተቋማትን በመገንባት አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የወረዳዋን የውሃ ሽፋን 63% ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡

ግብርና

ለም መሬቶች ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ያመርታሉ።

የእንስሳት እርባታ

የእንስሳት እርባታ ምግብ፣ ገቢ እና ወጎችን ያስቀጥላል።

ተፈጥሮ ሀብት

በለም አፈር፣ በውሃ አካላት እና በብዝሃ ህይወት የታደለች።

Discover

ቱሪዝም

ከጥንት የሐይማኖት ቦታዎች እስከ ባህላዊ ቱፊቶች ባለቤት

Awayitu hot spring, natural thermal wonder in Jille Timuga District

አዋይቱ ፍል ውሃ

አዋይቱ ፉል ዉሃ በዱላ፣ በወ/ሌንጫ እና በመረዋ አደሬ ቀበሌ አዋሳኝ ቀበሌዎች በ4 ተራሮች መካከል የሚገኝ ሲሆን ከሰንበቴ በግምት 4ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ፍልዉሃ በተፈጠሮ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በጣም ከሞመቁ የተነሳ አካባቢዉን በጭስ ስለሚሸፍን ለአካባቢዉ ልዩ ዉበት ሰቶታል፡፡ በአካባቢዉ አጠራር አዋይቱ የሚለዉ ከኦሮምኛ ቋንቋ ኦአ (o’aa) ከሚለዉ የመጣ ሲሆን ትረጉሙም ሙቅ የሞቀ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ፍልዉሃ ከመሬት ዉስጥ የሚወጣ ሲሆን 3 ትልልቅና 6 ትንንሽ የእንፋሎት መዉጫዎች አሉት፡፡ በነዚህ ቀዳዳዎች የሚወጣዉ ሃይለኛ ነጎድጓዳማ ድመፅ ከፈተኛ ነዉ፡፡የዉሃዉ ሙቀት በመሳሪያ ባይለካም ከሙቀቱ የተነሳ ወደ ዉሃዉ የሚያስጠጋ አይደለም፡፡

ፍል ዉሃዉ የሚገኘዉ በአራት ተራሮች መካከል ከሰንበቴ ከሚመጣዉ የቀቢ ወንዝና ከአጣዬ ከሚመጣዉ የአጣዬ ወንዝ መጋጠሚያ የዉስጥ አንግል ላይ፣ረግረጋማና ዛፎች ባሉበት እንዲሁም ከሞቀዉ ዉሃ በሚመጣ እንፋሎት በጭስ መልክ በታፈነ አካባቢ ነዉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን በአንድ ቦታና በአንድ ጊዜ ማየት ተፈጥሮን ለሚያደንቁ ከፍተኛ የመንፈስ እርካታን ይሰጣል፡፡

ፍልዉሃዉ በዘመናዊ መልክ ለምቶ አገልግሎት ባይሰጥም  ባለበት ሁኔታ  ህብረተሰቡ ለተለያዩ ነገሮች ይጠቀሙበታል ከነዚህም መካከል፡ ፍሉን ዉሃ ከወረጅ/ቀዝቃዛ ዉሃ ጋር በመበረዝ ሰዉነታቸዉን የሚታጠቡ ሲሆን እንዲሁም ጭሱን ደግሞ ይታጠኑበታል፡፡ይህም የሚሆንበት ምክንያት ከተያዩ በሽታዎች እንፈወሳልን የሚል እምነት ስላላቸዉ ነዉ፡፡

የሰንበቴ ገበያ

የሰንበቴ ገበያ ዘወትር እሁድ ቀን በሰንበቴ ከተማ የሚዉል ትልቅ ገበያ ነዉ፡፡ ከዛሬ 250 አመት በፊት በድጉጉሩ አካባቢ ነዋሪ የነበሩ ሃጂ ቡሽራ የሚባሉ ከፍተኛ የሃይማኖት መሪ የሆኑ ግለሰብ በአካባቢዉ ብ/ሰቦች መካከል ያለዉን ግጭት ለማስወገድ ይህ ከተማ ባለበት ቦታ ገበያ እዳቋቋሙ ይነገራል፡፡ የገበያዉ ቀንም በመጀመሪያ እሁድ እለት ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ገበያዋ ሰኞ እንዲሆን ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰኞ የስራ ቀን ስለሆነ እንደገና በደርግ ዘመን እሁድ እንዲሆን ተደረገ፡፡

የሰንበቴ ገበያ የብዙ ብሄሮች ስብጥር በመሆኗ ልዩ የትያትር መድረክ ያደርጋታል፡የኦሮሞ፣ አማራ፣ የአፋርና የአርጎባ ብሄረሰቦች ከነባህላዊ አለባበሳቸዉና አጋጌጣቸዉ በገበያዉ ሲገናኙ ለጎብኝዎች እንደሙዝየም አስደናቂ ሆነዉ ይገኛሉ፡፡ ባህላቸዉን የሚያዉቅ ሰዉ ያለአንዳች ችግር ማን የየትኛዉ ብሄር አባል እንደሆነ መናገር ይችላል፡፡ ይህ ብቻ አይደልም ይህን ገበያ የትያትር መድረክ ያስመሰለዉ፣ በገበያዉ ላይ የተለያዩ ባህላዊ ጌጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም የእደጥበብ ዉጤቶች በብዛት መታየታቸዉ ነዉ፡፡ የዉጭና የአገር ዉስጥ ቱሪስቶች እነዚህን ባህላዊ ጌጣጌጥና አልባሳትን ሲገዙ በስፋ ይታያሉ፡፡

ጥሩሲና መስጊድ

የእምነት ምልክት እና የስነ-ህንፃ ውበት።

ፌቂ-አቡስ መስጊድ

ጥልቅ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያለው ጥንታዊ መስጊድ

Heritage

ባህላዊ እሴቶች

የብዘሀ የባህል እሴቶች ባለቤትና የአብሮነት ተምሳሌት

ወደ መነሻ ገጽ

ባህላዊ አልባሳት

የማህበረሰቡን ማንነት፣ ጥበብ እና ኩራትን የሚያንፀባርቁ ደማቅ የባህል አልባሳት

Traditional Law of Wollo Oromo

ሴራ አባ ኦርማ

ሴረ አባ ኦርማ ቀጥተኛ ትርጉሙ የኦሮሞ አባት ህግ ማላት ሲሆን በወረዳው ውስጥ የገዳ ስርዓት በተለያየ ምክንያት ሲዳከምና ስራ ላይ ማዋል ባለመቻሉ የተፈጠረ ወይም የተመሰረተና በገዳ ስርዓት ምትክ የሚያገለግል የመተዳደርያ ህግ ነው፡፡ ይህም ስርዓት በሁለት ዋና ዋና ፈርጆች ተከፍሎ የሚታይ ይሆናል፡፡

አንዱና የመጀመሪያው ሴረ አባ ኦርማ ክፍል ጀላ ተብሎ የሚታወቅ ነው፡፡ጀላ ማለት ጥሬ ትርጉሙ ትልቅና ሰፊ አውራጎዳና እንደማለት ሲሆን ይህም ህጉ ተጽፎና ተሰንዶ የሚታይና የሚዳሰስ ባይሆንም ነገር ግን በእያንዳንዱ ትውልድ ጭንቅላት ውስጥ ለዘመናት የኖረና ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ ትልቅ ስርዓት ነው፡፡

ሁለተኛው የሴራ አባ ኦርማ ክፍል "Buuda/Baasa" በመባል የሚታወቅ ስርዓት ሲሆን በማህበረሰቡ ውስጥ ታይተውና ተሰምተው የማይታወቁ የተለያዩ የወንጀል ዓይነቶች ተከስተው ሲታዩ/ሲገኙ/ የሚዳኙበት ስርዓት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ በአይነቱ ለየት ያለ ወንጀል ተከስቶ ሲገኝ ሽማግሌዎች ተሰባስበው በመገናኘት ቁጭ ብለው እስቲ ይባባላሉ፡፡

እስቲ የሚለው ቃል ትርጉም የተከሰተው ወንጀል ከዚህ ቀደም ታይቶና ተሰምቶ የሚታወቅ ነወይ በማለት መጠያየቅና የንግግራቸው መንደርደሪያ የሚያደርጉት ቃል ነው፡፡ በመጨረሻም የተከሰተው ወንጀል በአካባቢውም ይሁን በሌላ አካባቢ ተክስቶ የሚታወቅ ሆኖ ከተገኘ በተከሰተበትና ከዚህ በፊት በተዳኘበት አግባብ የሚዳኝና የሚፈፀም ይሆናል፡፡ ይህ አይነት ስርዓት ከላይ እንደተጠቀሰው ጀላ በመባል ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ሽማግሌዎቹ ቁጭ ብለው ሲመክሩ የተከሰተው ወንጀል በአካባቢው ተሰምቶና ታይቶም የማይታወቅ ከሆነ ይህ ወንጀል ቡደ/ባሰ/ በመባል ይጠራል፡፡ በሌላ አነጋገር ትንግርት/ተዓምራዊ ክስተት/የሚል ትርጓሜ ይሰጠናል፡፡ ለዚህም ወንጀል የሚሰጠው ውሳኔ ልክ እንደ ክስተቱ አዲስነት ውሳኔውም በአይነቱ ለየት ያለ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ወንጀሉ ታይቶ የማይታወቅ፣ተሰምቶ የማያውቅና በተፈጸመው ወንጀል በ3 የወንጀል ዓይነቶች የሚቀጣ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ባህላዊ ምግቦች

ለተለያዩ ዝግጅቶች እና ለሀይማኖታዊ በዓላት የሚዘጋጁ የማህበረሰቡ መለያ የሆኑ ልዩ የባህል ምግቦች

Cultural Jewelry, Wollo Oromo

ባህላዊ ጌጣጌጦች

ዝግጅቶችን እና ክብረ በዓላትን የሚያስውቡ፣ ውበትን፣ ደረጃን እና ባህላዊ ማንነትን የሚያመለክቱ ጥንቃቄ የተሞላባቸው በእጅ የተሰሩ ጌጣጌጦች።

Traditional Reconciliation System of Wollo Oromo, Jille

ባህላዊ የእርቅ ስርዓት

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በውይይት እና በሽማግሌዎች ሽምግልና የሚከናወን ጥንታዊ የግጭት አፈታት ዘዴ።

Leadership

District Leadership

Aliy Seid Aliy

አልይ ሰይድ አልይ

District Chief Administrator

From: 26/01/2016

History

Former District Chief Administrators

መሀመድ አልይ ሀሰን

From: 11/11/2014 - To: 03/09/2015

አህመድ መሀመድ አብደላ

From: 28/04/2014 - To: 11/11/2014

አህመድ ሀሰን አልይ

From: 19/02/2014 - To: 27/04/2014

ጀማል ሀሰን መሀመድ

From: 01/04/2012 - To: 19/02/2014

አብደላ አህመድ መሀመድ

From: 19/11/2010 - To: 01/04/2012

ሙክታር አህመድ አብደላ

From: 16/04/2009 - To: 18/11/2010

ሙሄ ኡመር አብደላ

From: 26/10/2005 - To: 15/04/2009

መሀመድ ይማም

From: 01/11/2002 - To: 13/02/2004

ሰይድ ጃፈር አደም

From: - To:

መሀመድ አብዱ አህመድ

From: - To:

ደበሌ ዳዲ ሂርጳ

From: - To:

አህመድ መሀመድ ደዌ

From: - To:

Voice of Community

Share Your Feedback

We value your input. Help us improve our services and portal.