120K+ Population
4 Tourism Sites
7 Cultural Values
3 Languages
Our Story

ስለ ጅሌ

በታሪክ፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በባህላዊ ቱፊቶች የበለጸገ ማህበረሰብ

ታሪካዊ ዳራ

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የስም ስያሜዋን ያገኘችው የወረዳው ነዋሪዎች ከሆኑ ከአምስቱ ጅሌ እና ሱባ ጥሙጋ ሲሆን ጅሌም ሆነ ጥሙጋ በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ አባቶች ስም እንደሆነ ከሽማግሌዎችና እድሜ ጠገብ አባቶች የተገኙ ታሪኮች ያወሳሉ፡፡

ይህ ወረዳ በዚህ ስያሜ መጠራት የጀመረው በደርግ ስርዓተ መንግስት የወረዳዎችና ዞኖች ምስረታ ወቅት እንደሆነና በሰሜን ሸዋ ክፍላ ሀገር ይፋትና ዱሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ጅሌ ወረዳ በመባል እንደምትታወቅ የተለያዩ በጽሁፍ የሚገኙ ድርሳኖችና መጻጽፎች እንዲሁም አፈታሪኮች ያሰረዳሉ፡፡

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ይህን አሁን የምትጠራበትን ስያሜ ራሷን ችላ ያገኘችው ከ1986 ዓ/ም መባቻ ላይ ከኤፍራታና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ከተለየችበት ጊዜ አንስቶ ሲሆን የወረዳዋ ዋና ከተማ ሰንበቴ በማድረግ ተመሰረተች፡፡ በ1987 ዓ/ም የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ራሱን ችሎ በተመሰረተበት ወቅት ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጋር በመቀላቀል አርጡማ ጅሌ የሚል ስያሜ ተስጥቷት እስከ 1993 ዓ/ም መቆየቷም ይነገራል፡፡ የስሟ ስያሜ እንደየወቅቱና ነባራዊ ሁኔታ ሲቀያየር መጥቶ ከ1993 ዓ/ም መባቻ ላይ ከአርጡማ ጅሌ ወረዳ በመለየት ራሷን ችላ ዛሬ ለምትጠራበት ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ስያሜ ላይ ደርሳለች፡፡

እምነትና ቋንቋ

በወረዳዋ ውስጥ ከሚኖረው ማህበረሰብ 99% የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን 1% የሚሆኑት የተለያየ እምነት ተከታይ እንደሆኑ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ከቋንቋ አንፃር 95% ኦሮሚኛ ተናጋሪ ሲሆኑ 5% አማርኛ ተናጋሪ ናቸው፡፡

አካባቢ እና ስነ-ህዝብ

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የምትገኘው በአብክመ በኦሮሞ አስተዳደር ዞን ውስጥ በሰሜን ከአርጡማ ፉርሲ፣ በደቡብ ቀወት ወረዳና ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር፣በምዕራብ ኤፍራታ ግድምና ቀወት ወረዳ እንዲሁም በምስራቅ የአፋር ክልል ወረዳዎች ሀደለኢላና ሰሙ ሮቢ የምትዋሰን ሲሆን ከሀገራችንና መዲናችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ በስተሰሜን 265 ኪ.ሜ እርቃ ወደ ደሴ በሚወስደው በትልቁ አውራ መንገድ ላይ የትገኛለች፡፡ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር በስተምስራቅ 765 ኪ.ሜ እርቃ የምትገኝ ሲሆን፣ ከዞኑ መቀመጫ ከተማ ከሆነችው ከሚሴ በስተደቡብ በዋናው የደሴ አድስ አበባ መንገድ ላይ 63 ኪ.ሜ ላይ ትገኛለች፡፡

የአየር ሁኔታና የመሬት አቀማመጥ

የወረዳዋ አየር ንብርት 97% የሚሆነው በቆላማነት የሚታወቅ ሲሆን 3% የሚሆነው ወይና ደጋ ነው፡፡ የአየር ሙቀቷም ዝቅተኛው 240c ሲሆን ከፍተኛው 330c ነው፡፡ የወረዳዋ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ2,000- 2,600 ሚ. ሊ. እንደሆነ የወረዳዋ የአየር ንብረት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የዝናብ ወቅቶችም ክረምትና በልግ ሲሆን የክረምቱ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም የሚቆይ ሲሆን የበልጉ ወቅት ከየካቲት እስከ ሚያዚያ የሚቆይ ይሆናል፡፡ የወረዳዋ የመሬት ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ከ500-700 ሜ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ የወረዳዋ የቆዳ ስፋት 88,256 ሄ/ር ሲሆን የመሬት አቀማመጧም 31,052 ሄ/ር የሚሆነው ተራራማና ዳገታማ ሲሆን 57,204 ሄ/ር የሚሆነው ሜዳማ ነው፡፡ ከዚህ የመሬት አቀማመጥ ውስጥ 12,000 ሄ/ር የሚሆነው ለእርሻ መሬት የሚያገለግል ሲሆን 25,280 ሄ/ር የሚሆነው በደን ተሸፍኖ ይገኛል፡፡

የህዝብ ብዛትና የአኗኗር ሁኔታ

የሀገሪቱ የ1997 ዓ/ም ስታስቲክሳዊ የህዝብ ቆጠራ ውጤት (Census) መሰረት በማድረግ አሁን ላይ የወረዳዋ ህዝብ ቁጥር 65,873 ወንድ 67,479 ሴት በድምሩ 133,352 እንደሚሆን የገመታል፡፡ ከዚህ የህዝብ ቁጥር ውስጥ 88% የሚሆነው ኑሮውን በግብርና የሚመራ ሲሆን 12% የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማራ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ትምህርት ያለበት ሁኔታ

በትምህርት መስክ ወረዳው ከዘውዳዊ አገዛዝ ጀምሮ ለዘመናት ወደ ኋላ ቀርቶ የነበረና በዚህም ምክንያት ማህበረሰቡ ልጆቹን በወቅቱ ማስተማር ባለመቻሉ እንደ ማህበረሰብ ንቃተ ህሊናው በትምህርት የዳበረ ትውልድ የመፍጠር ራዕይ ጊዜ ሊወስድ እንደቻለ ማየት ተችሏል፡:

በመሆኑም ይህንን ጉድለት ለመሙላት በተሄደው ርቀትና በተሰራው ስራ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 3 የ2ኛ ደረጃ ት/ት ተቋም፣ 46 ከ1-8ኛ ክፍል ማስተማር የሚችሉ ተቋማትና እንዲሁም የቅድመ መደበኛ ት/ትን ጨምሮ በጥቅሉ 50 የትምህርት ተቋማትን በመገንባት መማር ካለባቸው 26,364 ህጻናት ውስጥ 20,264 ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በማድረግ የወረዳው የትምህርት ሽፋን 77% ላይ እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል፡፡

የጤና ዘርፍ

ጤናማ ማህበረሰባ በመፍጠር አምራች ዜጋን እውን የማድረግ ራዕይን በተግባር ለማሳየት መተሄደው ርቀት የጤና ተቋማትን በስታናዳርዱ መሰረት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚሁ አግባብ 4 ጤና ጣቢያዎች ተገንበተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደወረዳ 20 የጤና ኬላዎች መኖር ሲገባ 19 እንዲኖር ማድረግ ተችሏል፡፡ በጥቅሉ የተቋማት ማስፋፋት፣የግብዓት አቅርቦት፣የአገልግሎት አሰጣጥና የሰው ሀይል ስምሪትን ጨምሮ የተሳለጠ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በተሰራው ስራ የወረዳውን የጤና ሽፋን 86% ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡

ንጹህ ውሃ አቅርቦት

ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በተሄደው ርቀት 218 የውሃ ተቋማትን በመገንባት አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የወረዳዋን የውሃ ሽፋን 63% ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡

ግብርና

ለም መሬቶች ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ያመርታሉ።

የእንስሳት እርባታ

የእንስሳት እርባታ ምግብ፣ ገቢ እና ወጎችን ያስቀጥላል።

ተፈጥሮ ሀብት

በለም አፈር፣ በውሃ አካላት እና በብዝሃ ህይወት የታደለች።

Discover

ቱሪዝም

ከጥንት የሐይማኖት ቦታዎች እስከ ባህላዊ ቱፊቶች ባለቤት

ወደ መነሻ ገጽ

ጥሩሲና መስጊድ

የእምነት ምልክት እና የስነ-ህንፃ ውበት።

Awayitu hot spring, natural thermal wonder in Jille Timuga District

አዋይቱ ፍል ውሃ

አዋይቱ ፉል ዉሃ በዱላ፣ በወ/ሌንጫ እና በመረዋ አደሬ ቀበሌ አዋሳኝ ቀበሌዎች በ4 ተራሮች መካከል የሚገኝ ሲሆን ከሰንበቴ በግምት 4ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ፍልዉሃ በተፈጠሮ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በጣም ከሞመቁ የተነሳ አካባቢዉን በጭስ ስለሚሸፍን ለአካባቢዉ ልዩ ዉበት ሰቶታል፡፡ በአካባቢዉ አጠራር አዋይቱ የሚለዉ ከኦሮምኛ ቋንቋ ኦአ (o’aa) ከሚለዉ የመጣ ሲሆን ትረጉሙም ሙቅ የሞቀ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ፍልዉሃ ከመሬት ዉስጥ የሚወጣ ሲሆን 3 ትልልቅና 6 ትንንሽ የእንፋሎት መዉጫዎች አሉት፡፡ በነዚህ ቀዳዳዎች የሚወጣዉ ሃይለኛ ነጎድጓዳማ ድመፅ ከፈተኛ ነዉ፡፡የዉሃዉ ሙቀት በመሳሪያ ባይለካም ከሙቀቱ የተነሳ ወደ ዉሃዉ የሚያስጠጋ አይደለም፡፡

ፍል ዉሃዉ የሚገኘዉ በአራት ተራሮች መካከል ከሰንበቴ ከሚመጣዉ የቀቢ ወንዝና ከአጣዬ ከሚመጣዉ የአጣዬ ወንዝ መጋጠሚያ የዉስጥ አንግል ላይ፣ረግረጋማና ዛፎች ባሉበት እንዲሁም ከሞቀዉ ዉሃ በሚመጣ እንፋሎት በጭስ መልክ በታፈነ አካባቢ ነዉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን በአንድ ቦታና በአንድ ጊዜ ማየት ተፈጥሮን ለሚያደንቁ ከፍተኛ የመንፈስ እርካታን ይሰጣል፡፡

ፍልዉሃዉ በዘመናዊ መልክ ለምቶ አገልግሎት ባይሰጥም  ባለበት ሁኔታ  ህብረተሰቡ ለተለያዩ ነገሮች ይጠቀሙበታል ከነዚህም መካከል፡ ፍሉን ዉሃ ከወረጅ/ቀዝቃዛ ዉሃ ጋር በመበረዝ ሰዉነታቸዉን የሚታጠቡ ሲሆን እንዲሁም ጭሱን ደግሞ ይታጠኑበታል፡፡ይህም የሚሆንበት ምክንያት ከተያዩ በሽታዎች እንፈወሳልን የሚል እምነት ስላላቸዉ ነዉ፡፡

የሰንበቴ ገበያ

የሰንበቴ ገበያ ዘወትር እሁድ ቀን በሰንበቴ ከተማ የሚዉል ትልቅ ገበያ ነዉ፡፡ ከዛሬ 250 አመት በፊት በድጉጉሩ አካባቢ ነዋሪ የነበሩ ሃጂ ቡሽራ የሚባሉ ከፍተኛ የሃይማኖት መሪ የሆኑ ግለሰብ በአካባቢዉ ብ/ሰቦች መካከል ያለዉን ግጭት ለማስወገድ ይህ ከተማ ባለበት ቦታ ገበያ እዳቋቋሙ ይነገራል፡፡ የገበያዉ ቀንም በመጀመሪያ እሁድ እለት ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ገበያዋ ሰኞ እንዲሆን ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰኞ የስራ ቀን ስለሆነ እንደገና በደርግ ዘመን እሁድ እንዲሆን ተደረገ፡፡

የሰንበቴ ገበያ የብዙ ብሄሮች ስብጥር በመሆኗ ልዩ የትያትር መድረክ ያደርጋታል፡የኦሮሞ፣ አማራ፣ የአፋርና የአርጎባ ብሄረሰቦች ከነባህላዊ አለባበሳቸዉና አጋጌጣቸዉ በገበያዉ ሲገናኙ ለጎብኝዎች እንደሙዝየም አስደናቂ ሆነዉ ይገኛሉ፡፡ ባህላቸዉን የሚያዉቅ ሰዉ ያለአንዳች ችግር ማን የየትኛዉ ብሄር አባል እንደሆነ መናገር ይችላል፡፡ ይህ ብቻ አይደልም ይህን ገበያ የትያትር መድረክ ያስመሰለዉ፣ በገበያዉ ላይ የተለያዩ ባህላዊ ጌጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም የእደጥበብ ዉጤቶች በብዛት መታየታቸዉ ነዉ፡፡ የዉጭና የአገር ዉስጥ ቱሪስቶች እነዚህን ባህላዊ ጌጣጌጥና አልባሳትን ሲገዙ በስፋ ይታያሉ፡፡

ፌቂ-አቡስ መስጊድ

ጥልቅ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያለው ጥንታዊ መስጊድ

Heritage

ባህላዊ እሴቶች

የብዘሀ የባህል እሴቶች ባለቤትና የአብሮነት ተምሳሌት

Traditional Law of Wollo Oromo

ሴራ አባ ኦርማ

ሴረ አባ ኦርማ ቀጥተኛ ትርጉሙ የኦሮሞ አባት ህግ ማላት ሲሆን በወረዳው ውስጥ የገዳ ስርዓት በተለያየ ምክንያት ሲዳከምና ስራ ላይ ማዋል ባለመቻሉ የተፈጠረ ወይም የተመሰረተና በገዳ ስርዓት ምትክ የሚያገለግል የመተዳደርያ ህግ ነው፡፡ ይህም ስርዓት በሁለት ዋና ዋና ፈርጆች ተከፍሎ የሚታይ ይሆናል፡፡

አንዱና የመጀመሪያው ሴረ አባ ኦርማ ክፍል ጀላ ተብሎ የሚታወቅ ነው፡፡ጀላ ማለት ጥሬ ትርጉሙ ትልቅና ሰፊ አውራጎዳና እንደማለት ሲሆን ይህም ህጉ ተጽፎና ተሰንዶ የሚታይና የሚዳሰስ ባይሆንም ነገር ግን በእያንዳንዱ ትውልድ ጭንቅላት ውስጥ ለዘመናት የኖረና ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ ትልቅ ስርዓት ነው፡፡

ሁለተኛው የሴራ አባ ኦርማ ክፍል "Buuda/Baasa" በመባል የሚታወቅ ስርዓት ሲሆን በማህበረሰቡ ውስጥ ታይተውና ተሰምተው የማይታወቁ የተለያዩ የወንጀል ዓይነቶች ተከስተው ሲታዩ/ሲገኙ/ የሚዳኙበት ስርዓት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ በአይነቱ ለየት ያለ ወንጀል ተከስቶ ሲገኝ ሽማግሌዎች ተሰባስበው በመገናኘት ቁጭ ብለው እስቲ ይባባላሉ፡፡

እስቲ የሚለው ቃል ትርጉም የተከሰተው ወንጀል ከዚህ ቀደም ታይቶና ተሰምቶ የሚታወቅ ነወይ በማለት መጠያየቅና የንግግራቸው መንደርደሪያ የሚያደርጉት ቃል ነው፡፡ በመጨረሻም የተከሰተው ወንጀል በአካባቢውም ይሁን በሌላ አካባቢ ተክስቶ የሚታወቅ ሆኖ ከተገኘ በተከሰተበትና ከዚህ በፊት በተዳኘበት አግባብ የሚዳኝና የሚፈፀም ይሆናል፡፡ ይህ አይነት ስርዓት ከላይ እንደተጠቀሰው ጀላ በመባል ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ሽማግሌዎቹ ቁጭ ብለው ሲመክሩ የተከሰተው ወንጀል በአካባቢው ተሰምቶና ታይቶም የማይታወቅ ከሆነ ይህ ወንጀል ቡደ/ባሰ/ በመባል ይጠራል፡፡ በሌላ አነጋገር ትንግርት/ተዓምራዊ ክስተት/የሚል ትርጓሜ ይሰጠናል፡፡ ለዚህም ወንጀል የሚሰጠው ውሳኔ ልክ እንደ ክስተቱ አዲስነት ውሳኔውም በአይነቱ ለየት ያለ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ወንጀሉ ታይቶ የማይታወቅ፣ተሰምቶ የማያውቅና በተፈጸመው ወንጀል በ3 የወንጀል ዓይነቶች የሚቀጣ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ባህላዊ አልባሳት

የማህበረሰቡን ማንነት፣ ጥበብ እና ኩራትን የሚያንፀባርቁ ደማቅ የባህል አልባሳት

ባህላዊ ምግቦች

ለተለያዩ ዝግጅቶች እና ለሀይማኖታዊ በዓላት የሚዘጋጁ የማህበረሰቡ መለያ የሆኑ ልዩ የባህል ምግቦች

Cultural Jewelry, Wollo Oromo

ባህላዊ ጌጣጌጦች

ዝግጅቶችን እና ክብረ በዓላትን የሚያስውቡ፣ ውበትን፣ ደረጃን እና ባህላዊ ማንነትን የሚያመለክቱ ጥንቃቄ የተሞላባቸው በእጅ የተሰሩ ጌጣጌጦች።

Traditional Reconciliation System of Wollo Oromo, Jille

ባህላዊ የእርቅ ስርዓት

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በውይይት እና በሽማግሌዎች ሽምግልና የሚከናወን ጥንታዊ የግጭት አፈታት ዘዴ።

Latest Updates

ዜና እና ልጥፎች

ትኩስ መረጃዎችንና ማስታወቂያዎችን ይከታተሉ።

May 10, 2026

እየተከናወኑ ያሉ የመስኖ ልማቶች

በወረዳው ስራ ባሉ ቀበሌዎች የመስኖ ልማት እንቅስቃሴ እጅግ አመርቂ ውጤቶችን በማምጣት ላይ ነው፡፡
May 10, 2026

የህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረክ

በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን አጎራባች ወረዳና ከተማ አስተዳደር የህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረክ በጀዋሀ ከተማ ተካሄደ:: በአካባቢው የልማትና የሰላም እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ችግር ለመፍታት የክልልና የዞን አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።የነበረውን የሰላምና የልማት ስራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና እየታዩ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ያለመ ውይይት መሆኑን በመድረኩ ተገልፇል።የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ድረስ ሳህሉ እና የክልሉ ምክትል ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ኮምሺነር ደጀኔ ልመንህ ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ በመድረኩ ተገኝተው ተሳታፊዎችን አወያይተዋል።እንዲሁም የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ አሊ ሰይድ ፣የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሪት ፋጡማ ሀሰን ፣የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አበራ መኮነን ፣ እና ሌሎች የወረዳና የዞን እንዲሁም የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው የሁለቱም ዞን አጎራባች ወረዳ ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል።
May 10, 2026

የፌድራልና የክልል ባለስልጣናት ጉብኝት

በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ እና በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የፌድራል ሚንስቴር እና የክልል ቢሮ ሃላፊዎች እዲሁም የዞን ከፍተኛ አመራሮች በወረዳው የተሰሩ የልማት ስራዎችንና የቱሪስት መስህቦችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል። የፌድራል ቆላማ መስኖ ሚኒስቴር ሚንተር ዶክተር አብራሃም በላይ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው በሰንበቴም ሆነ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር ያሉትን ችግሮች ለይተው ዘላቂ መፍትሄ በመስጠት የልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደመጡ ተናግረዋል። በቀጣይ በዞኑም ይሁን በወረዳ ደረጃ ያሉ ችግሮችን ለይተን በመያዝ በፌድራልም ሆነ በክልል ደረጃ ምላሽ የሚያገኙትን የመልካም አስተደሰደር ችግሮች እንፈታለን በማለት ነው ቃል የገቡት። የክልልና የፌድራል ባለስልጣናቶች በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ወረ ሌንጫ ቀበሌ በመሄድ የአዋይቱን ፍሉሃ ጨምሮ ፣በአላላ ቀበሌ የመስኖ ስራዎች እንዲሁም የተሰሩ የገጠር መንገዶችን ጉብኝት አድርገዋል። በመጨረሻም የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር ለከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናቶችና ለክልል ቢሮ ሃላፊዎች ባህላዊ አልባሳት እና የእርድ በሬ ሽልማት በማበርከት ፕሮገራሙ ተጠናቋል። ‎ ‎ በመስመልክ ምልከታውና በፕሮግራሙ ላይ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ሀብታሙ ኢተፋ ፣የቆላ መስኖ ሚኒስቴር ዶክተር አብራሃም በላይ ፣በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
Leadership

District Leadership

አልይ ሰይድ አልይ

District Chief Administrator

From: 26/01/2016

Former Chief Administrator

Former District Chief Administrators

Voice of Community

Share Your Feedback

We value your input. Help us improve our services and portal.