በትምህርት መስክ ወረዳው ከዘውዳዊ አገዛዝ ጀምሮ ለዘመናት ወደ ኋላ ቀርቶ የነበረና በዚህም ምክንያት ማህበረሰቡ ልጆቹን በወቅቱ ማስተማር ባለመቻሉ እንደ ማህበረሰብ ንቃተ ህሊናው በትምህርት የዳበረ ትውልድ የመፍጠር ራዕይ ጊዜ ሊወስድ እንደቻለ ማየት ተችሏል፡፡ በመሆኑም ይህንን ጉድለት ለመሙላት በተሄደው ርቀትና በተሰራው ስራ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 3 የ2ኛ ደረጃ ት/ት ተቋም፣ 461-8ኛ ክፍል ማስተማር የሚችሉ ተቋማትና እንዲሁም የቅድመ መደበኛ ት/ትን ጨምሮ በጥቅሉ 50 የትምህርት ተቋማትን በመገንባት መማር ካለባቸው 26,364 ህጻናት ውስጥ 20,264 ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በማድረግ የወረዳው የትምህርት ሽፋን 77% ላይ እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል፡፡